Opera አሳሽ ለAndroid መሳሪያዎ፣ እንደ አዲስ የተሰራ የዜና ምግብ፣ በውስጥ የተገነባ የማስታወቂያ ማገጃ እና ነጻ VPN ያለው፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የድር አሳሽ ነው።
★ ውና ባህሪያት ★
● ለፈጣን አሰሳ ማስታወቂያዎችን ያግዱ፦
የOpera የራሱ የማስታወቂያ አጋጅ ጣልቃ ገብ ማስታወቂያዎችን እንዲያስወግዱ ይረዳዎታል እንዲሁም የአሰሳ ተሞክሮዎን እንዲያቀላጥፉ ገጾችዎ በፍጥነት ይጭናል።
● ነጻ፣ ያልተገደበ፣ በውስጥ የተገነባ VPN፦
ግላዊነትዎን እና ደህንነትዎን በውስጥ በተገነባ እና ነጻ በሆነው VPN ያሻሽሉ። Opera VPNን በግል ሁነታ ውስጥ ይክፈ��ት ከዚያም ሳያስቡት የአካባቢዎን እና ማንነትን የሚያሳውቅ መረጃ ከማጋራት ለመቆጠብ እንዲረዳዎ የIP አድራሻዎ በሌላ ቨርቹዋል IP ይተካል።
● የውስጥ ሰር QR እና ባርኮድ መቃኛ ፡
የውስጥ ሰር QR እና ባርኮድ መቃኛ በቀላሉ ይደረሱ። የፍለጋ ትሩን መታ ያድርጉ እና መቃኘው በቀኝ በኩል የሚገኝ ይሆናል። ካሜራዎን በማንኛውም QR-ኮድ/ባርኮድ ላይ ይጠቁሙ እና በራስ ሰር ይቃኛል።
● Flow፡ በቀላሉ ሁሉንም መሳሪያዎችዎን ያገናኛል ፡
በእርስዎ iPhone, Android ስልክ፣ ታብሌት እና ኮምፒዩተር መካከል በቀላሉ መቀየር በሚይስችልዎ መልኩ ታዋቂው የFlow ባህርይ ያተጋሯቸው ፋልይሎችን፣ አገናኞችን፣ ወይም ምስሎችን በሁሉም Flow በነቃባቸውን መሳሪያዎች ላይ በቅጽበት እንዲታዩ ያደርጋል።
● ግላዊነት የተላበሰ የዜና ምግብ፦
እጅግ ብልህ በሆነው AI የዜና ፍርግማችን፣ ዳግም የተጀመረ የዜና ምግብ ለግልዎ የተመረጡ የዜና ጣቢያዎችን በአሳሹ ውስጥ እንዲያስሱ፣ ለተወዳጅ ርዕሶችዎ እንዲመዘገቡ፣ እንዲሁም ዘገባዎችን በኋላ ለማንበብ እንዲያስቀምጡ ያስችልዎታል። በተለይ ለእርስዎፍላጎት የተዘጋጁ በAI የተጠናቀሩ ዜናዎችን ያግኙ።
● የሌሊት ሁነታ፦
የOpera የሌሊት ሁነታ፣ በአይን ላይ የሚያስከትለውን ውጥረት በመቀነስ መስተካከል የሚችሉ የብርሃን መጠን አማራጮችን በማቅረብ በጨለማ ውስጥ ምቹ የሆነ ተሞክሮ ይሰጥዎታል። የሌሊት ሁነታ ከዋናው ምናሌ በቀላሉ ይደረስበታል።
● የይለፍ ቃሎችን ያስተዳድሩ እንዲሁም ክሬዲት ካርዶችን በራስ ሰር ይሙሉ፦
የይለፍ ቃላት በራስ ሰር እንዲቀመጡ ይምረጡ እንዲሁም ለመስመር ላይ ግብይት የክፍያ መረጃዎን አደጋ የለሽ በሆነ አኳኋን በራስ-ሰር ይሙሉ።
● ግላዊነቱ የተጠበቀ አሰሳ፦
● በመሳሪያዎ ላይ ምንም ዱካ ሳይተዉ ማንነትዎን ሳያሳውቁ በይነመረብን ለማሰስ ግላዊ ትርን ይጠቀሙ። በትር ጋለሪ ውስጥ ማንነትን በማያሳውቅ እና በመደበኛ የአሰሳ ሁነታ መካከል በቀላሉ ይቀያይሩ።
● በማንኛውም ማያ ገጽ ላይ በምቾት ያንብቡ፦
Opera አሳሽ እንደ ንባብ ምርጫዎ ገጾችን ለማስማማት የሚረዳዎ የጽሁፍ መጠን ቅንብርን አካትቷል። ከዚህም በላይ፣ ተወዳዳሪ ለሌለው የንባብ ተሞክሮ ከእኛ የራስ-ሰር ጽሁፍ ማጠፍ በትክክል ይሰራል።
● ውርዶችን በቀላሉ ያስተዳድሩ፦
አዲሱ የማውረድ አስተዳዳሪያችን ፋይሎችን ማውረድን ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ቀላል እና ፈጣን አድርጎታል! በቀላሉ መደርደር እና እያንዳንዱን የወረደ ንጥል ማጋራት፣ ከስልክዎ መሰረዝ ወይም ከውርዶች ዝርዝር ውስጥ በፍጥነት ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ በማንሸራተት ማስወገድ ይችላሉ። ማውረዱ እየተካሄድ ነገር ግን ሌላ መተግበሪያ ��ክፈት ቢያስፈልግዎ ከበስተጀርባ ማውረድንም እንኳን እንደግፋለን!
● የመነሻ ማያ ገጽ አቋራጮች፦
በAndroid ስሪት 7.1 ወይም ከዚያ በላይ የሚግኝ ሲሆን፣ Opera አሳሽ ከመነሻ ማያ ገጽ ለፍለጋ፣ አዲስ የግል ትር ለመክፈት፣ ወይም QR ኮዶችን ለመቃኘት ፈጣን መዳረሻ ይሰጣል። የራስዎን መነሻ አቋራጭ ለመፍጠር፣ በመሳሪያዎ መነሻ ገጽ ላይ ያለው የ Opera አዶን መታ አድርገው ይያዙ ከዚያም የሚፈልጉትን ተግባር መታ ያድርጉ።
ሌሎች ማድመቂያዎች
● አሳሽን ማስጀመሪያ አማራቾች፦
ሁሉም ሰው ግለሰብ ነው፣ ስለዚህ አሳሹን ሁልጊዜ በአዲስ ትር የመክፈት ወይም ካቆምበት አሰሳዎን ለመቀጠልም እንዲሁም አሳሹን ለቀው በሚወጡ ጊዜ የተከፈቱ ትሮችዎን ለመዝጋት ወይም ለማቆየት እንዲመርጡ ምርጫውን ለእርስዎ እንሰጥዎታለን።
● Opera መሳሪያዎችዎን ያመሳስሉ፦
ለራስዎ ወደ ሁሉም እልባቶችዎ፣ ፈጣን መደወያ አቋራጮች እና የተከፈቱ ትሮ�� ከሌሎች መሳሪያዎችዎ በOpera መዳረሻዎችን ይስጡ። Opera በAndroid ላይ አሁን በቀላሉ ከOpera አሳሽ ለኮምፒውተሮች ጋር በቀላሉ መመሳሰል ይችላል።
● ወደ መነሻ ገጽ ያክሉ፦
ማንኛውንም ድር ጣቢያ ከዚህም በበለጠ በፍጥነት ለማግኘት በቀጥታ ወደ መሳሪያዎ መነሻ ገጽ ያክሉት። እንደ Facebook ያሉ ጣቢያዎች ተገፊ ማሳወቂያዎችንም ሊልኩልዎ ይችላሉ፣ የሚጠበቅብዎ መተግበሪያውን መውደድ ብቻ ነው።
በOpera የበለጠ ይስሩ፥ http://www.opera.com/about/products/
Opera Mini ከ Facebook ማስታወቂያዎችን ሊያሳይ ይችላል። የበለጠ ለማወቅ፣ https://m.facebook.com/ads/ad_choices ይመልክቱ
ከእኛ ጋር በቅርበት ይቆዩ፦
Twitter – http://twitter.com/opera/
Facebook – http://www.facebook.com/opera/
Instagram – http://www.instagram.com/opera
የስምምነት ነጥቦችና አስገዳጅ ሁኔታዎች
ይህንን መተግበርያ በማውረድ የ https://www.opera.com/eula/mobile ተጠቃሚ ፍቃድ ስምምነት ተስማምተዋል ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ የርስዎ ውሂብ እንዴት እንደሚይዝና እንደሚጠብቅ https://www.opera.com/privacy ላይ ከሚገኝ የ Opera ግለኝነት መግለጫ ማወቅ ይችላሉ፡፡